-
ማቴዎስ 13:39አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
39 እንክርዳዱን የዘራው ጠላት፣ ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዚህ ሥርዓት* መደምደሚያ ሲሆን አጫጆቹ ደግሞ መላእክት ናቸው።
-
-
ማርቆስ 13:3, 4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በቤተ መቅደሱ ትይዩ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ ብቻቸውን ሆነው እንዲህ በማለት ጠየቁት፦ 4 “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የእነዚህ ነገሮች ሁሉ መደምደሚያ መቅረቡን የሚያሳየው ምልክትስ ምንድን ነው?”+
-
-
ሉቃስ 21:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 እነሱም “መምህር፣ እነዚህ ነገሮች በእርግጥ የሚፈጸሙት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙበትን ጊዜ የሚጠቁመው ምልክትስ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+
-