1 ተሰሎንቄ 5:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ስለዚህ ነቅተን እንኑር+ እንዲሁም የማስተዋል ስሜታችንን እንጠብቅ+ እንጂ እንደ ሌሎቹ አናንቀላፋ።+ 1 ጴጥሮስ 5:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የማስተዋል ስሜታችሁን ጠብቁ፤ ንቁ ሆናችሁ ኑሩ!+ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይንጎራደዳል።+