ማርቆስ 14:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።+ 11 እነሱም ይህን ሲሰሙ ደስ አላቸውና የብር ገንዘብ* ሊሰጡት ቃል ገቡለት።+ ስለዚህ እሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር። ሉቃስ 22:3-6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከዚያም ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ሆኖ በተቆጠረውና አስቆሮቱ ተብሎ በሚጠራው በይሁዳ ሰይጣን ገባበት፤+ 4 ይሁዳም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደሱ ሹሞች ሄዶ ኢየሱስን ለእነሱ አሳልፎ መስጠት ስለሚችልበት መንገድ ተነጋገረ።+ 5 እነሱም በጉዳዩ ተደስተው የብር ገንዘብ* ሊሰጡት ተስማሙ።+ 6 እሱም በዚህ ተስማምቶ ሕዝብ በሌለበት እሱን አሳልፎ መስጠት የሚችልበትን ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር።
10 ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።+ 11 እነሱም ይህን ሲሰሙ ደስ አላቸውና የብር ገንዘብ* ሊሰጡት ቃል ገቡለት።+ ስለዚህ እሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር።
3 ከዚያም ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ሆኖ በተቆጠረውና አስቆሮቱ ተብሎ በሚጠራው በይሁዳ ሰይጣን ገባበት፤+ 4 ይሁዳም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደሱ ሹሞች ሄዶ ኢየሱስን ለእነሱ አሳልፎ መስጠት ስለሚችልበት መንገድ ተነጋገረ።+ 5 እነሱም በጉዳዩ ተደስተው የብር ገንዘብ* ሊሰጡት ተስማሙ።+ 6 እሱም በዚህ ተስማምቶ ሕዝብ በሌለበት እሱን አሳልፎ መስጠት የሚችልበትን ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር።