-
ማርቆስ 14:17-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 እሱም ከመሸ በኋላ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ።+ 18 በማዕድ ተቀምጠው እየበሉ ሳለም ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ፣ ከእኔ ጋር እየበላ ያለ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።+ 19 እነሱም አዝነው በየተራ “እኔ እሆን?” ይሉት ጀመር። 20 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይኸውም ከእኔ ጋር በሳህኑ ውስጥ የሚያጠቅሰው ነው።+ 21 የሰው ልጅ ስለ እሱ በተጻፈው መሠረት ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!+ ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።”+
-
-
ሉቃስ 22:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ሰዓቱ በደረሰ ጊዜም ከሐዋርያቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።+
-