-
ማርቆስ 14:32-36አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
32 ከዚያም ጌትሴማኒ ወደተባለ ቦታ መጡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም “እኔ በምጸልይበት ጊዜ እናንተ እዚህ ተቀመጡ” አላቸው።+ 33 ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ከእሱ ጋር ይዟቸው ሄደ፤+ ከዚያም እጅግ ይጨነቅና* ይረበሽ ጀመር። 34 ኢየሱስም “እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ።*+ እዚህ ሁኑና ነቅታችሁ ጠብቁ”+ አላቸው። 35 ትንሽ ወደ ፊት ራቅ በማለት መሬት ላይ ተደፍቶ ቢቻል ሰዓቱ ከእሱ እንዲያልፍ ይጸልይ ጀመር። 36 እንዲህም አለ፦ “አባ፣* አባት ሆይ፣+ አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ ትችላለህ፤ ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ። ሆኖም እኔ የምፈልገው ሳይሆን አንተ የምትፈልገው ይሁን።”+
-
-
ሉቃስ 22:40አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
40 እዚያም በደረሱ ጊዜ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ” አላቸው።+
-