14 ወንድሞች፣ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ያላቸውን በይሁዳ የሚገኙትን የአምላክ ጉባኤዎች ምሳሌ ተከትላችኋል፤ ምክንያቱም እነሱ በአይሁዳውያን እጅ መከራ እየተቀበሉ እንዳሉ ሁሉ እናንተም በገዛ አገራችሁ ሰዎች እጅ ተመሳሳይ መከራ ተቀብላችኋል፤+ 15 አይሁዳውያን ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ሳይቀር የገደሉ+ ከመሆኑም በላይ በእኛ ላይ ስደት አድርሰዋል።+ ከዚህም በተጨማሪ አምላክን እያስደሰቱ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሰውን ሁሉ ጥቅም የሚጻረሩ ናቸው፤