-
ሉቃስ 8:28-30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
28 ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እየጮኸ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም “የልዑል አምላክ ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለ።+ 29 (ይህን ያለውም ኢየሱስ ርኩሱ መንፈስ ከሰውየው እንዲወጣ እያዘዘው ስለነበረ ነው። ርኩሱ መንፈስ ሰውየውን ብዙ ጊዜ ይይዘው ነበር፤*+ ሰውየው በተደጋጋሚ በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም የታሰረበትን ሰንሰለት ይበጣጥስ ነበር፤ ጋኔኑም ጭር ወዳሉ ቦታዎች ይነዳው ነበር።) 30 ኢየሱስ “ስምህ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ስለነበር “ሌጌዎን” አለው።
-