-
ሉቃስ 8:51-56አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
51 ወደ ኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቷ አባትና እናት በስተቀር ማንም አብሮት ወደ ውስጥ እንዲገባ አልፈቀደም። 52 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ ለልጅቷ እያለቀሱና በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ “በቃ አታልቅሱ፤+ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም”+ አላቸው። 53 ይህን ሲሰሙ ልጅቷ እንደሞተች ያውቁ ስለነበር በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። 54 እሱ ግን እጇን በመያዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” አለ።+ 55 የልጅቷም መንፈስ*+ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሳች፤+ የምትበላውም ነገር እንዲሰጧት አዘዘ። 56 ወላጆቿም የሚሆኑት ጠፋቸው፤ እሱ ግን የሆነውን ነገር ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።+
-