-
ማቴዎስ 13:54-58አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
54 ወደ ትውልድ አገሩ+ ከመጣ በኋላ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ጀመር፤ ሰዎቹም ተገርመው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና እነዚህን ተአምራት የማድረግ ችሎታ ከየት አገኘ?+ 55 ይህ የአናጺው ልጅ አይደለም?+ እናቱስ ማርያም አይደለችም? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉም?+ 56 እህቶቹስ ሁሉ የሚኖሩት ከእኛ ጋር አይደለም? ታዲያ ይህን ሁሉ ከየት አገኘው?”+ 57 ከዚህም የተነሳ ተሰናከሉበት።+ ኢየሱስ ግን “ነቢይ በገዛ አገሩና በገዛ ቤቱ ካልሆነ በስተቀር በሌላ ቦታ ሁሉ ይከበራል” አላቸው።+ 58 በእሱ ባለማመናቸው በዚያ ብዙ ተአምራት አልፈጸመም።
-