-
ማቴዎስ 14:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 በዚያን ጊዜ የአውራጃ ገዢ* የነበረው ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሲሰማ+ 2 አገልጋዮቹን “ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው። ከሞት ተነስቷል ማለት ነው፤ እነዚህን ተአምራት መፈጸም የቻለውም ለዚህ ነው” አላቸው።+ 3 ሄሮድስ* የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት በሆነችው በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን ይዞ በሰንሰለት በማሰር ወህኒ አስገብቶት ነበር።+ 4 ዮሐንስ ሄሮድስን “እሷን እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር።+ 5 ሄሮድስ ሊገድለው ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሕዝቡ እንደ ነቢይ ይመለከተው ስለነበር ሕዝቡን ፈራ።+
-