ማቴዎስ 9:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 እነሆም፣ ለ12 ዓመት ደም ይፈሳት የነበረች አንዲት ሴት+ ከኋላ መጥታ የልብሱን ዘርፍ ነካች፤+ ማርቆስ 5:25-28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈሳት+ የኖረች አንዲት ሴት ነበረች።+ 26 ይህች ሴት በርካታ ሐኪሞች ጋር የሄደች ሲሆን ሕክምናው ለብዙ ሥቃይ ዳርጓት ነበር፤ ያላትን ጥሪት ሁሉ ብትጨርስም ሕመሙ ባሰባት እንጂ አልተሻላትም። 27 ስለ ኢየሱስ የተወራውን በሰማች ጊዜ በሰዎች መካከል ከኋላው መጥታ ልብሱን ነካች፤+ 28 ምክንያቱም “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ” ብላ ታስብ ነበር።+ ሉቃስ 8:43, 44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈስሳት+ የኖረች አንዲት ሴት የነበረች ሲሆን ይህችን ሴት ሊፈውሳት የቻለ አንድም ሰው አልነበረም።+ 44 ከኋላም መጥታ የልብሱን ዘርፍ ነካች፤+ ይፈሳት የነበረውም ደም ወዲያውኑ ቆመ። የሐዋርያት ሥራ 19:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 አምላክም በጳውሎስ እጅ በጣም አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን መፈጸሙን ቀጠለ፤+ 12 ሰዎችም የጳውሎስን ሰውነት የነኩ ጨርቆችንና ሽርጦችን ወደታመሙት ሰዎች ሲወስዱ+ ሰዎቹ በሽታቸው ይለቃቸው ነበር፤ ርኩሳን መናፍስትም ይወጡ ነበር።+
25 በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈሳት+ የኖረች አንዲት ሴት ነበረች።+ 26 ይህች ሴት በርካታ ሐኪሞች ጋር የሄደች ሲሆን ሕክምናው ለብዙ ሥቃይ ዳርጓት ነበር፤ ያላትን ጥሪት ሁሉ ብትጨርስም ሕመሙ ባሰባት እንጂ አልተሻላትም። 27 ስለ ኢየሱስ የተወራውን በሰማች ጊዜ በሰዎች መካከል ከኋላው መጥታ ልብሱን ነካች፤+ 28 ምክንያቱም “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ” ብላ ታስብ ነበር።+
43 በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈስሳት+ የኖረች አንዲት ሴት የነበረች ሲሆን ይህችን ሴት ሊፈውሳት የቻለ አንድም ሰው አልነበረም።+ 44 ከኋላም መጥታ የልብሱን ዘርፍ ነካች፤+ ይፈሳት የነበረውም ደም ወዲያውኑ ቆመ።
11 አምላክም በጳውሎስ እጅ በጣም አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን መፈጸሙን ቀጠለ፤+ 12 ሰዎችም የጳውሎስን ሰውነት የነኩ ጨርቆችንና ሽርጦችን ወደታመሙት ሰዎች ሲወስዱ+ ሰዎቹ በሽታቸው ይለቃቸው ነበር፤ ርኩሳን መናፍስትም ይወጡ ነበር።+