3 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ትእዛዝ የምትጥሱት ለምንድን ነው?+ 4 ለምሳሌ አምላክ ‘አባትህንና እናትህን አክብር’+ እንዲሁም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል’ ብሏል።+ 5 እናንተ ግን እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን “እናንተን መጦር የምችልበት፣ ያለኝ ነገር ሁሉ ለአምላክ የተወሰነ ስጦታ ነው”+ ካለ 6 አባቱን የማክበር ግዴታ የለበትም።’ በመሆኑም ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ቃል ሽራችኋል።+