-
ማቴዎስ 15:15-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 ጴጥሮስም መልሶ “ምሳሌውን አብራራልን” አለው። 16 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተም እስካሁን ማስተዋል ተስኗችኋል?+ 17 ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ እንደሚዘልቅና ከዚያም ወጥቶ ወደ ጉድጓድ እንደሚገባ አታውቁም? 18 ይሁን እንጂ ከአፍ የሚወጣ ሁሉ ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ይህ ነው።+ 19 ለምሳሌ ከልብ ክፉ ሐሳብ ይወጣል፦+ ግድያ፣ ምንዝር፣ የፆታ ብልግና፣* ሌብነት፣ በሐሰት መመሥከርና ስድብ። 20 ሰውን የሚያረክሱት እነዚህ ነገሮች ናቸው፤ እጅን ሳይታጠቡ* መብላት ግን ሰውን አያረክስም።”
-