-
ማቴዎስ 17:14-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ወደ ሕዝቡ በመጡ ጊዜ+ አንድ ሰው ወደ እሱ ቀረበና ተንበርክኮ እንዲህ አለው፦ 15 “ጌታ ሆይ፣ ለልጄ ምሕረት አድርግለት፤ የሚጥል በሽታ ስላለበት በጠና ታሟል። አንዴ እሳት ውስጥ አንዴ ደግሞ ውኃ ውስጥ ይወድቃል።+ 16 ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት፤ እነሱ ግን ሊፈውሱት አልቻሉም።” 17 ኢየሱስም መልሶ “እምነት የለሽና ጠማማ ትውልድ ሆይ፣+ ከእናንተ ጋር እስከ መቼ መቆየት ሊኖርብኝ ነው? እስከ መቼስ እናንተን መታገሥ ሊኖርብኝ ነው? ልጁን ወደ እኔ አምጡት” አለ።
-