ማቴዎስ 24:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፤+ 5 ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ።+ ሉቃስ 21:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እሱም እንዲህ አለ፦ “እንዳያሳስቷችሁ ተጠንቀቁ፤+ ብዙዎች ‘እኔ እሱ ነኝ’ እንዲሁም ‘ጊዜው ቀርቧል’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና። እነሱን አትከተሉ።+