ዘፀአት 24:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በመሆኑም ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፤+ እንዲህም አለ፦ “በእነዚህ ቃላት መሠረት ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ደም ይህ ነው።”+ ዘሌዋውያን 17:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ምክንያቱም የሥጋ ሕይወት* ያለው በደሙ ውስጥ ነው፤+ ለራሳችሁም* ማስተሰረያ እንዲሆን እኔ ራሴ ደሙን ለእናንተ ስል ለመሠዊያው ሰጥቼዋለሁ፤+ ምክንያቱም በውስጡ ባለው ሕይወት* አማካኝነት የሚያስተሰርየው ደሙ ነው።+ ዕብራውያን 9:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 አዎ፣ በሕጉ መሠረት ሁሉም ነገር ማለት ይቻላል በደም ይነጻል፤+ ደም ካልፈሰሰ በስተቀር ይቅርታ ማግኘት አይቻልም።+
11 ምክንያቱም የሥጋ ሕይወት* ያለው በደሙ ውስጥ ነው፤+ ለራሳችሁም* ማስተሰረያ እንዲሆን እኔ ራሴ ደሙን ለእናንተ ስል ለመሠዊያው ሰጥቼዋለሁ፤+ ምክንያቱም በውስጡ ባለው ሕይወት* አማካኝነት የሚያስተሰርየው ደሙ ነው።+