-
ማቴዎስ 26:42-46አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
42 እንደገናም ሄዶ ለሁለተኛ ጊዜ “አባቴ ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ሳልጠጣው ይለፍ። ካልሆነ ግን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም”+ ሲል ጸለየ። 43 ዳግመኛም ተመልሶ ሲመጣ እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ስለነበር ተኝተው አገኛቸው። 44 እንደገናም ትቷቸው ሄደና ለሦስተኛ ጊዜ ስለዚያው ነገር ደግሞ ጸለየ። 45 ከዚያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ የእንቅልፍና የእረፍት ሰዓት ነው? እነሆ፣ የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ የሚሰጥበት ሰዓት ደርሷል። 46 ተነሱ፣ እንሂድ። እነሆ፣ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል።”
-