መዝሙር 22:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤ሰው ያፌዘብኝ፣* ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።+ ኢሳይያስ 53:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ግፍ ተፈጸመበት፤+ መከራም ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነ፤+ነገር ግን አፉን አልከፈተም። እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤+በሸላቾቿ ፊት ዝም እንደምትል በግ፣እሱም አፉን አልከፈተም።+ ዳንኤል 9:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “ከ62ቱ ሳምንታት በኋላ መሲሑ ይቆረጣል፤*+ ትቶት የሚያልፈው ምንም ነገር አይኖርም።+ “የሚመጣውም መሪ ሠራዊት፣ ከተማዋንና ቅዱሱን ስፍራ ያጠፋል።+ ፍጻሜው በጎርፍ ይሆናል። እስከ ፍጻሜውም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተወስኗል።+ ሉቃስ 22:37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 ይህን የምላችሁ ‘ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ’+ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ላይ መፈጸም ስላለበት ነው። ስለ እኔ የተነገረው ነገር ፍጻሜውን እያገኘ ነውና።”+
7 ግፍ ተፈጸመበት፤+ መከራም ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነ፤+ነገር ግን አፉን አልከፈተም። እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤+በሸላቾቿ ፊት ዝም እንደምትል በግ፣እሱም አፉን አልከፈተም።+
26 “ከ62ቱ ሳምንታት በኋላ መሲሑ ይቆረጣል፤*+ ትቶት የሚያልፈው ምንም ነገር አይኖርም።+ “የሚመጣውም መሪ ሠራዊት፣ ከተማዋንና ቅዱሱን ስፍራ ያጠፋል።+ ፍጻሜው በጎርፍ ይሆናል። እስከ ፍጻሜውም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተወስኗል።+