-
ማቴዎስ 27:27-31አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 በዚህ ጊዜ የአገረ ገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ አገረ ገዢው መኖሪያ ቤት ወሰዱት፤ ሠራዊቱንም ሁሉ በዙሪያው አሰባሰቡ።+ 28 ልብሱንም ገፈው ቀይ መጎናጸፊያ አለበሱት፤+ 29 የእሾህ አክሊል ጎንጉነውም በራሱ ላይ ደፉበት፤ በቀኝ እጁም የመቃ ዘንግ አስያዙት። በፊቱ ተንበርክከውም “የአይሁዳውያን ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ አሾፉበት። 30 ደግሞም ተፉበት፤+ መቃውንም ወስደው ራሱን ይመቱት ጀመር። 31 ሲያፌዙበት ከቆዩ በኋላም መጎናጸፊያውን ገፈው የራሱን መደረቢያዎች አለበሱት፤ ከዚያም በእንጨት ላይ እንዲቸነከር ይዘውት ሄዱ።+
-