33 የራስ ቅል ቦታ የሚል ትርጉም ወዳለው ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ+ በደረሱ ጊዜ 34 ሐሞት የተቀላቀለበት የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤+ እሱ ግን ከቀመሰው በኋላ ሊጠጣው አልፈለገም። 35 እንጨት ላይ ከቸነከሩት በኋላ ዕጣ ተጣጥለው መደረቢያዎቹን ተከፋፈሉ፤+ 36 በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር። 37 እንዲሁም “ይህ የአይሁዳውያን ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የተከሰሰበትን ጉዳይ የሚገልጽ ጽሑፍ ከራሱ በላይ አንጠልጥለው ነበር።+