-
መዝሙር 22:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤
በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።+
-
-
ዮሐንስ 19:23, 24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ወታደሮቹ ኢየሱስን በእንጨት ላይ ከቸነከሩት በኋላ መደረቢያዎቹን ወስደው እያንዳንዱ ወታደር አንድ አንድ ቁራጭ እንዲደርሰው አራት ቦታ ቆራረጧቸው፤ ከውስጥ ለብሶት የነበረውንም ልብስ ወሰዱ። ሆኖም ልብሱ ከላይ እስከ ታች አንድ ወጥ ሆኖ ያለስፌት የተሠራ ነበር። 24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው “ከምንቀደው ዕጣ ተጣጥለን ለማን እንደሚደርስ እንወስን” ተባባሉ።+ ይህም የሆነው “መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤ በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” የሚለው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።+ ወታደሮቹም ያደረጉት ይህንኑ ነበር።
-