መዝሙር 22:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የሚያዩኝ ሁሉ ያላግጡብኛል፤+በንቀትና በፌዝ ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ እንዲህ ይሉኛል፦+ መዝሙር 109:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 የእነሱ መሳለቂያ ሆንኩ።+ ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።+ ኢሳይያስ 53:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሰዎች የናቁትና ያገለሉት፣+ሥቃይን ያየ፣* ሕመምንም የሚያውቅ ሰው ነበር። ፊቱ የተሰወረብን ያህል ነበር።* ሰዎች ናቁት፤ እኛም ከቁብ አልቆጠርነውም።+