46 በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ “ኤሊ፣ ኤሊ፣ ላማ ሳባቅታኒ?” ብሎ ጮኸ፤ ይህም “አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው።+ 47 በዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ “ይህ ሰው ኤልያስን እየተጣራ ነው” ይሉ ጀመር።+ 48 ወዲያውኑም ከመካከላቸው አንዱ ሮጦ በመሄድ ሰፍነግ ወስዶ የኮመጠጠ የወይን ጠጅ ውስጥ ከነከረ በኋላ በመቃ ላይ አድርጎ እንዲጠጣ ሰጠው።+ 49 የቀሩት ግን “ተወው! ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደሆነ እንይ” አሉ።