-
ማርቆስ 1:23-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 በዚሁ ጊዜ በምኩራባቸው ውስጥ የነበረ፣ ርኩስ መንፈስ የያዘው አንድ ሰው በኃይል ጮኾ እንዲህ አለ፦ 24 “የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን?+ የመጣኸው ልታጠፋን ነው? ማን እንደሆንክ በሚገባ አውቃለሁ፤ አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ ነህ!”+ 25 ሆኖም ኢየሱስ “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። 26 ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእሱ ወጣ። 27 ሕዝቡ ሁሉ እጅግ በመገረም እርስ በርሳቸው “ይህ ምንድን ነው? ትምህርቱ ለየት ያለ ነው! ርኩሳን መናፍስትን እንኳ ሳይቀር በሥልጣን ያዛል፤ እነሱም ይታዘዙለታል” ተባባሉ። 28 ወዲያውኑም በመላው የገሊላ ግዛት በየአቅጣጫው ስለ እሱ በስፋት ተወራ።
-