ማቴዎስ 8:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት ሲመጣ የጴጥሮስ አማት+ ትኩሳት ይዟት ተኝታ አገኛት።+ 15 እጇንም ሲዳስሳት+ ትኩሳቱ ለቀቃት፤ ተነስታም ታገለግለው ጀመር። ማርቆስ 1:29-31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 በዚህ ጊዜ ከምኩራብ ወጥተው ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት ሄዱ።+ 30 የስምዖን አማት+ ትኩሳት ይዟት ተኝታ ነበር፤ ስለ እሷም ወዲያው ለኢየሱስ ነገሩት። 31 እሱም ወደተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሳት። በዚህ ጊዜ ትኩሳቱ ለቀቃትና ታገለግላቸው ጀመር።
29 በዚህ ጊዜ ከምኩራብ ወጥተው ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት ሄዱ።+ 30 የስምዖን አማት+ ትኩሳት ይዟት ተኝታ ነበር፤ ስለ እሷም ወዲያው ለኢየሱስ ነገሩት። 31 እሱም ወደተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሳት። በዚህ ጊዜ ትኩሳቱ ለቀቃትና ታገለግላቸው ጀመር።