6 ኢየሱስ ይህን ሰው በዚያ ተኝቶ አየውና ለረጅም ጊዜ ሕመምተኛ ሆኖ እንደኖረ አውቆ “መዳን ትፈልጋለህ?”+ አለው። 7 ሕመምተኛውም “ጌታዬ፣ ውኃው በሚናወጥበት ጊዜ ገንዳው ውስጥ የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፤ ወደ ገንዳው ስሄድ ደግሞ ሌላው ቀድሞኝ ይገባል” ሲል መለሰለት። 8 ኢየሱስም “ተነስ! ምንጣፍህን ተሸክመህ ሂድ” አለው።+ 9 ሰውየውም ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ ምንጣፉንም አንስቶ መሄድ ጀመረ።
ቀኑም ሰንበት ነበር።