1 ነገሥት 17:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ከዚያም ልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ከተዘረጋበት በኋላ “አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ የዚህ ልጅ ሕይወት ይመለስለት”* ብሎ ወደ ይሖዋ ጮኸ። 22 ይሖዋም የኤልያስን ልመና ሰማ፤+ የልጁም ሕይወት ተመለሰለት፤* እሱም ሕያው ሆነ።+ ሉቃስ 8:52-54 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 52 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ ለልጅቷ እያለቀሱና በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ “በቃ አታልቅሱ፤+ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም”+ አላቸው። 53 ይህን ሲሰሙ ልጅቷ እንደሞተች ያውቁ ስለነበር በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። 54 እሱ ግን እጇን በመያዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” አለ።+ ዮሐንስ 11:43 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 ይህን ከተናገረ በኋላ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ።+ የሐዋርያት ሥራ 9:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ+ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች።+
21 ከዚያም ልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ከተዘረጋበት በኋላ “አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ የዚህ ልጅ ሕይወት ይመለስለት”* ብሎ ወደ ይሖዋ ጮኸ። 22 ይሖዋም የኤልያስን ልመና ሰማ፤+ የልጁም ሕይወት ተመለሰለት፤* እሱም ሕያው ሆነ።+
52 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ ለልጅቷ እያለቀሱና በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ “በቃ አታልቅሱ፤+ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም”+ አላቸው። 53 ይህን ሲሰሙ ልጅቷ እንደሞተች ያውቁ ስለነበር በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። 54 እሱ ግን እጇን በመያዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” አለ።+
40 ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ+ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች።+