-
ማቴዎስ 11:7-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 መልእክተኞቹ ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ይናገር ጀመር፦ “ወደ ምድረ በዳ የሄዳችሁት ምን ለማየት ነበር?+ ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆ?+ 8 ታዲያ ምን ለማየት ነበር የሄዳችሁት? ምርጥ ልብስ* የለበሰ ሰው ለማየት? ምርጥ ልብስ የለበሱማ የሚገኙት በነገሥታት ቤት ነው። 9 ታዲያ ለምን ሄዳችሁ? ነቢይ ለማየት? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጥ ነው።+ 10 ‘እነሆ፣ ከፊትህ እየሄደ መንገድህን እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ!’+ ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ነው። 11 እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።+
-