ኢሳይያስ 40:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አንድ ሰው በምድረ በዳ እንዲህ ብሎ ይጮኻል፦ “የይሖዋን መንገድ ጥረጉ!*+ በበረሃ ለአምላካችን አውራ ጎዳናውን+ አቅኑ።+ ሚልክያስ 3:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 “እነሆ፣ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ እሱም በፊቴ መንገድ ይጠርጋል።*+ እናንተ የምትፈልጉት እውነተኛው ጌታ* በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤+ ደስ የምትሰኙበት የቃል ኪዳኑ መልእክተኛም ይመጣል። እነሆ፣ እሱ በእርግጥ ይመጣል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። ሉቃስ 1:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ከእስራኤል ልጆች መካከልም ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ* ይመልሳል።+ 17 በተጨማሪም ሰዎችን ለይሖዋ * ያዘጋጅ ዘንድ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ ለማድረግ፣*+ የማይታዘዙትንም ሰዎች ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ በኤልያስ መንፈስና ኃይል+ በአምላክ ፊት ይሄዳል።”+ ዮሐንስ 1:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 እሱም “ነቢዩ ኢሳይያስ እንደተናገረው ‘የይሖዋን* መንገድ አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኸው ሰው እኔ ነኝ” አለ።+
3 “እነሆ፣ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ እሱም በፊቴ መንገድ ይጠርጋል።*+ እናንተ የምትፈልጉት እውነተኛው ጌታ* በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤+ ደስ የምትሰኙበት የቃል ኪዳኑ መልእክተኛም ይመጣል። እነሆ፣ እሱ በእርግጥ ይመጣል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
16 ከእስራኤል ልጆች መካከልም ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ* ይመልሳል።+ 17 በተጨማሪም ሰዎችን ለይሖዋ * ያዘጋጅ ዘንድ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ ለማድረግ፣*+ የማይታዘዙትንም ሰዎች ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ በኤልያስ መንፈስና ኃይል+ በአምላክ ፊት ይሄዳል።”+