-
ማቴዎስ 13:20, 21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 በድንጋያማ መሬት ላይ የተዘራው ደግሞ ቃሉን ሲሰማ ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበል ሰው ነው።+ 21 ሆኖም ቃሉ በውስጡ ሥር ስለማይሰድ የሚቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ በቃሉ የተነሳም መከራ ወይም ስደት ሲደርስበት ወዲያው ይሰናከላል።
-
-
ማርቆስ 4:16, 17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 በተመሳሳይም በድንጋያማ መሬት እንደተዘሩት ዘሮች የሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉን እንደሰሙ በደስታ ይቀበሉታል።+ 17 ሆኖም ቃሉ በውስጣቸው ሥር ስለማይሰድ የሚቆዩት ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያም በቃሉ የተነሳ መከራ ወይም ስደት ሲደርስባቸው ወዲያውኑ ይሰናከላሉ።
-