ማቴዎስ 13:55 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 55 ይህ የአናጺው ልጅ አይደለም?+ እናቱስ ማርያም አይደለችም? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉም?+ ዮሐንስ 7:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ወንድሞቹም ቢሆኑ አላመኑበትም ነበር።+ የሐዋርያት ሥራ 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እነዚህ ሁሉ ከአንዳንድ ሴቶችና+ ከኢየሱስ እናት ከማርያም እንዲሁም ከወንድሞቹ+ ጋር በአንድ ልብ ተግተው ይጸልዩ ነበር።