-
ማቴዎስ 8:30-34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ከእነሱ ራቅ ብሎ ብዙ የአሳማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር።+ 31 አጋንንቱም “የምታስወጣን ከሆነ ወደ አሳማው መንጋ ስደደን” ብለው ይማጸኑት ጀመር።+ 32 እሱም “ሂዱ!” አላቸው። እነሱም ወጥተው ወደ አሳማዎቹ ሄዱ፤ የአሳማውም መንጋ በሙሉ ከገደሉ አፋፍ* እየተንደረደረ በመውረድ ባሕሩ ውስጥ ሰጥሞ አለቀ። 33 እረኞቹ ግን ሸሽተው ወደ ከተማው በመሄድ አጋንንት ባደሩባቸው ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጨምሮ የሆነውን ነገር ሁሉ አወሩ። 34 ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ለማግኘት ወጣ፤ ሰዎቹም ባዩት ጊዜ አካባቢያቸውን ለቆ እንዲሄድ ለመኑት።+
-
-
ማርቆስ 5:11-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 በዚያም በተራራው ላይ ብዙ የአሳማ+ መንጋ ተሰማርቶ ነበር።+ 12 ርኩሳን መናፍስቱም “አሳማዎቹ ውስጥ እንድንገባ ወደ እነሱ ስደደን” ብለው ተማጸኑት። 13 እሱም ፈቀደላቸው። በዚህ ጊዜ ርኩሳን መናፍስቱ ወጥተው አሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ወደ 2,000 የሚጠጉ አሳማዎችም ከገደሉ አፋፍ* እየተንደረደሩ በመውረድ ባሕሩ ውስጥ ሰጠሙ። 14 የአሳማዎቹ እረኞች ግን ሸሽተው በመሄድ ወሬውን በከተማውና በገጠሩ አዳረሱ፤ ሰዎችም የሆነውን ነገር ለማየት መጡ።+ 15 ወደ ኢየሱስም መጥተው ጋኔን ያደረበትን ይኸውም ቀደም ሲል ሌጌዎን የነበረበትን ሰው ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ተቀምጦ አዩት፤ በዚህ ጊዜ ፍርሃት አደረባቸው። 16 የተፈጸመውንም ነገር ያዩ ሰዎች አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደቻለና በአሳማዎቹ ላይ የሆነውን ነገር አወሩላቸው። 17 በመሆኑም አካባቢያቸውን ለቆ እንዲሄድ ኢየሱስን ይማጸኑት ጀመር።+
-