ማቴዎስ 9:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ይህን እየነገራቸው ሳለ አንድ የምኩራብ አለቃ ወደ እሱ መጥቶ በመስገድ* “እስካሁን ልጄ ሳትሞት አትቀርም፤ ቢሆንም መጥተህ እጅህን ጫንባት፤ ዳግመኛም ሕያው ትሆናለች”+ አለው። 19 ኢየሱስም ተነስቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው። ማርቆስ 5:22-24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 በዚህ ጊዜ ከምኩራብ አለቆች አንዱ የሆነ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው ወደዚያ መጣ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እግሩ ላይ ወደቀ።+ 23 ከዚያም “ትንሿ ልጄ በጠና ታምማለች።* እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር፣ እባክህ መጥተህ እጅህን ጫንባት”+ በማለት ደጋግሞ ተማጸነው። 24 ኢየሱስም አብሮት ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሕዝብም ተከትሎት እየተጋፋው ይሄድ ነበር።
18 ይህን እየነገራቸው ሳለ አንድ የምኩራብ አለቃ ወደ እሱ መጥቶ በመስገድ* “እስካሁን ልጄ ሳትሞት አትቀርም፤ ቢሆንም መጥተህ እጅህን ጫንባት፤ ዳግመኛም ሕያው ትሆናለች”+ አለው። 19 ኢየሱስም ተነስቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው።
22 በዚህ ጊዜ ከምኩራብ አለቆች አንዱ የሆነ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው ወደዚያ መጣ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እግሩ ላይ ወደቀ።+ 23 ከዚያም “ትንሿ ልጄ በጠና ታምማለች።* እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር፣ እባክህ መጥተህ እጅህን ጫንባት”+ በማለት ደጋግሞ ተማጸነው። 24 ኢየሱስም አብሮት ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሕዝብም ተከትሎት እየተጋፋው ይሄድ ነበር።