-
ማቴዎስ 18:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው ማን ነው?” አሉት።+ 2 ኢየሱስም አንድ ትንሽ ልጅ ጠርቶ በመካከላቸው በማቆም 3 እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ካልተመለሳችሁና* እንደ ልጆች ካልሆናችሁ+ በምንም ዓይነት ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም።+ 4 ስለዚህ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው እንደዚህ ትንሽ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው፤+ 5 እንዲሁም እንደዚህ ያለውን ትንሽ ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል።
-
-
ማርቆስ 9:33-37አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
33 ከዚህ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። ወደ ቤት ከገባም በኋላ “በመንገድ ላይ ስትከራከሩ የነበረው ስለ ምን ጉዳይ ነው?”+ ሲል ጠየቃቸው። 34 በመንገድ ላይ እርስ በርስ የተከራከሩት “ከሁላችን የሚበልጠው ማን ነው?” በሚል ስለነበረ ዝም አሉ። 35 ስለዚህ ከተቀመጠ በኋላ አሥራ ሁለቱን ጠርቶ “መጀመሪያ መሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉም መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ መሆን አለበት” አላቸው።+ 36 ከዚያም አንድ ትንሽ ልጅ አምጥቶ በመካከላቸው አቆመ፤ አቅፎትም እንዲህ አላቸው፦ 37 “እንዲህ ካሉት ልጆች+ አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ እኔን ብቻ ሳይሆን የላከኝንም ይቀበላል።”+
-
-
ሉቃስ 22:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ደግሞም ‘ከመካከላችን ታላቅ የሆነው ማን ነው?’ በሚል በመካከላቸው የጦፈ ክርክር ተነሳ።+
-