43 “ርኩስ መንፈስ ከሰው ሲወጣ የሚያርፍበት ቦታ ፍለጋ ውኃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ ሆኖም የሚያርፍበት ቦታ አያገኝም።+ 44 ከዚያም ‘ወደለቀቅኩት ቤቴ ተመልሼ እሄዳለሁ’ ይላል፤ ሲመለስም ቤቱ ባዶ ሆኖ፣ ጸድቶና አጊጦ ያገኘዋል። 45 ከዚያም ሄዶ ከእሱ የከፉ ሌሎች ሰባት መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውም ይኖሩበታል፤ የዚያም ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከቀድሞው የከፋ ይሆንበታል።+ ይህ ክፉ ትውልድም ተመሳሳይ ነገር ይደርስበታል።”