2 ዜና መዋዕል 24:20, 21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 የአምላክ መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ+ ልጅ በዘካርያስ ላይ ወረደ፤ እሱም በሕዝቡ ፊት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ቆሞ እንዲህ አላቸው፦ “እውነተኛው አምላክ እንዲህ ይላል፦ ‘የይሖዋን ትእዛዛት የምትተላለፉት ለምንድን ነው? አይሳካላችሁም! ይሖዋን ስለተዋችሁ እሱም ይተዋችኋል።’”+ 21 እነሱ ግን በእሱ ላይ አሴሩ፤+ ንጉሡም በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በይሖዋ ቤት ግቢ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት።+ ነህምያ 9:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+
20 የአምላክ መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ+ ልጅ በዘካርያስ ላይ ወረደ፤ እሱም በሕዝቡ ፊት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ቆሞ እንዲህ አላቸው፦ “እውነተኛው አምላክ እንዲህ ይላል፦ ‘የይሖዋን ትእዛዛት የምትተላለፉት ለምንድን ነው? አይሳካላችሁም! ይሖዋን ስለተዋችሁ እሱም ይተዋችኋል።’”+ 21 እነሱ ግን በእሱ ላይ አሴሩ፤+ ንጉሡም በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በይሖዋ ቤት ግቢ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት።+
26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+