-
ማቴዎስ 22:41-46አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
41 ፈሪሳውያን አንድ ላይ ተሰብስበው እንዳሉ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦+ 42 “ስለ መሲሑ* ምን ትላላችሁ? የማን ልጅ ነው?” እነሱም “የዳዊት” አሉት።+ 43 እሱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “ታዲያ ዳዊት በመንፈስ ተመርቶ+ እንዴት ጌታ ብሎ ይጠራዋል? 44 ምክንያቱም ዳዊት ‘ይሖዋ* ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው’ ሲል ተናግሯል።+ 45 ታዲያ ዳዊት ጌታ ብሎ ከጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል?”+ 46 ከዚህ በኋላ አንዲት ቃል ሊመልስለት የቻለም ሆነ ከዚያ ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ አንድም ሰው አልነበረም።
-