-
ማቴዎስ 26:18, 19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 እሱም “ወደ ከተማ ሄዳችሁ እገሌ የተባለውን ሰው፣ ‘መምህሩ “የተወሰነው ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በቤትህ አከብራለሁ” ብሏል’ በሉት” አላቸው። 19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።
-
-
ማርቆስ 14:13-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 እሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦ “ወደ ከተማው ሂዱ፤ በዚያም የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። እሱንም ተከተሉት፤+ 14 ወደሚገባበት ቤት ሄዳችሁ የቤቱን ጌታ ‘መምህሩ “ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሏል’ በሉት። 15 እሱም የተነጠፈና የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል። እዚያ አዘጋጁልን።” 16 ደቀ መዛሙርቱም ሄዱ፤ ወደ ከተማውም ገቡ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።
-