ዕብራውያን 9:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የፍየሎችና የኮርማዎች ደም+ እንዲሁም በረከሱ ሰዎች ላይ የሚረጭ የጊደር አመድ ሥጋን በማንጻት የሚቀድስ ከሆነ+ 14 በዘላለማዊ መንፈስ አማካኝነት ራሱን ያላንዳች እንከን ለአምላክ ያቀረበው የክርስቶስ ደም+ ሕያው ለሆነው አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንድናቀርብ+ ሕሊናችንን ከሞቱ ሥራዎች እንዴት አብልጦ አያነጻም?+ 1 ጴጥሮስ 1:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 እናንተ ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት* ከንቱ አኗኗር ነፃ የወጣችሁት*+ ሊበላሹ በሚችሉ ነገሮች ይኸውም በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁና። 19 ከዚህ ይልቅ ነፃ የወጣችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ+ ደም ባለ ውድ ደም+ ይኸውም በክርስቶስ ደም ነው።+
13 የፍየሎችና የኮርማዎች ደም+ እንዲሁም በረከሱ ሰዎች ላይ የሚረጭ የጊደር አመድ ሥጋን በማንጻት የሚቀድስ ከሆነ+ 14 በዘላለማዊ መንፈስ አማካኝነት ራሱን ያላንዳች እንከን ለአምላክ ያቀረበው የክርስቶስ ደም+ ሕያው ለሆነው አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንድናቀርብ+ ሕሊናችንን ከሞቱ ሥራዎች እንዴት አብልጦ አያነጻም?+
18 እናንተ ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት* ከንቱ አኗኗር ነፃ የወጣችሁት*+ ሊበላሹ በሚችሉ ነገሮች ይኸውም በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁና። 19 ከዚህ ይልቅ ነፃ የወጣችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ+ ደም ባለ ውድ ደም+ ይኸውም በክርስቶስ ደም ነው።+