የሐዋርያት ሥራ 10:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 በተጨማሪም አምላክ እሱን በሕያዋንና በሙታን ላይ ፈራጅ አድርጎ እንደሾመው+ ለሰዎች እንድንሰብክና በተሟላ ሁኔታ* እንድንመሠክር አዘዘን።+ የሐዋርያት ሥራ 17:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ምክንያቱም በሾመው ሰው አማካኝነት በዓለም ሁሉ ላይ በጽድቅ ለመፍረድ+ ዓላማ ያለው ሲሆን ይህን ለማድረግም ቀን ወስኗል፤ እሱንም ከሞት በማስነሳት ለሰዎች ሁሉ ዋስትና ሰጥቷል።”+ 2 ቆሮንቶስ 5:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ምክንያቱም እያንዳንዱ በሥጋ እያለ ላደረገው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር፣ እንደ ሥራው ብድራት እንዲቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ልንቀርብ* ይገባል።+ 2 ጢሞቴዎስ 4:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በአምላክ ፊት እንዲሁም በሕያዋንና በሙታን+ ላይ በሚፈርደው+ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አጥብቄ አሳስብሃለሁ፤ ደግሞም በእሱ መገለጥና+ በመንግሥቱ+ አማካኝነት አዝሃለሁ፦
31 ምክንያቱም በሾመው ሰው አማካኝነት በዓለም ሁሉ ላይ በጽድቅ ለመፍረድ+ ዓላማ ያለው ሲሆን ይህን ለማድረግም ቀን ወስኗል፤ እሱንም ከሞት በማስነሳት ለሰዎች ሁሉ ዋስትና ሰጥቷል።”+
10 ምክንያቱም እያንዳንዱ በሥጋ እያለ ላደረገው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር፣ እንደ ሥራው ብድራት እንዲቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ልንቀርብ* ይገባል።+
4 በአምላክ ፊት እንዲሁም በሕያዋንና በሙታን+ ላይ በሚፈርደው+ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አጥብቄ አሳስብሃለሁ፤ ደግሞም በእሱ መገለጥና+ በመንግሥቱ+ አማካኝነት አዝሃለሁ፦