-
ማቴዎስ 28:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ስለዚህ ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ተውጠው ከመታሰቢያ መቃብሩ በፍጥነት በመውጣት ወሬውን ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር እየሮጡ ሄዱ።+
-
-
ሉቃስ 24:39-41አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
39 እኔ ራሴ መሆኔን እንድታውቁ እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ ደግሞም ዳስሳችሁኝ እዩ፤ መንፈስ በእኔ ላይ እንደምታዩት ሥጋና አጥንት የለውምና።” 40 ይህን እያለም እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። 41 እነሱ ግን በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ለማመን ተቸግረው በነገሩ እየተገረሙ ሳሉ “የሚበላ ነገር አላችሁ?” አላቸው።
-