ዮሐንስ 14:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 የዚህ ዓለም ገዢ+ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር ብዙ አልነጋገርም፤ እሱም በእኔ ላይ ምንም ኃይል የለውም።+ የሐዋርያት ሥራ 14:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 በዚያም “በብዙ መከራ አልፈን ወደ አምላክ መንግሥት መግባት አለብን”+ እያሉ በእምነት ጸንተው እንዲኖሩ በማበረታታት ደቀ መዛሙርቱን* አጠናከሩ።+ 1 ዮሐንስ 4:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ልጆቼ ሆይ፣ እናንተ ከአምላክ ወገን ናችሁ፤ እነሱንም* አሸንፋችኋል፤+ ምክንያቱም ከእናንተ ጎን ያለው፣+ ከዓለም ጎን ካለው ይበልጣል።+ 1 ዮሐንስ 5:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ምክንያቱም ከአምላክ የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል።+ ዓለምን ድል እንድናደርግ ያስቻለን እምነታችን ነው።+ ራእይ 3:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 እኔ ድል ነስቼ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥኩ ሁሉ+ ድል የሚነሳውንም+ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።+