39 ሴትየዋ “ያደረግኩትን ሁሉ ነገረኝ”+ ብላ ስለመሠከረች ከዚያች ከተማ ብዙ ሳምራውያን በእሱ አመኑ። 40 ሳምራውያኑም ወደ እሱ በመጡ ጊዜ አብሯቸው እንዲቆይ ለመኑት፤ እሱም በዚያ ሁለት ቀን ቆየ። 41 በመሆኑም ሌሎች ብዙ ሰዎች ከተናገረው ቃል የተነሳ አመኑ፤ 42 ሴትየዋንም “ከእንግዲህ የምናምነው አንቺ ስለነገርሽን ብቻ አይደለም፤ ምክንያቱም እኛ ራሳችን ሰምተናል፤ እንዲሁም ይህ ሰው በእርግጥ የዓለም አዳኝ+ እንደሆነ አውቀናል” አሏት።