32 “በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው ከታላቁ ስምህ፣ ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ፣+ ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ፣+ 33 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና+ እንዲፈሩህ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት።