-
የሐዋርያት ሥራ 10:10-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ይሁን እንጂ በጣም ከመራቡ የተነሳ መብላት ፈለገ። ምግብ እየተዘጋጀ ሳለም ሰመመን ውስጥ ገባ፤+ 11 ሰማይም ተከፍቶ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራቱም ጫፍ ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤ 12 በላዩም የተለያዩ በምድር ላይ የሚኖሩ አራት እግር ያላቸው እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታት እንዲሁም የሰማይ ወፎች ነበሩ። 13 ከዚያም አንድ ድምፅ “ጴጥሮስ፣ ተነሳና አርደህ ብላ!” አለው። 14 ጴጥሮስ ግን “ጌታ ሆይ፣ በጭራሽ፤ ምክንያቱም እኔ ንጹሕ ያልሆነና የረከሰ ነገር በልቼ አላውቅም” አለ።+ 15 ያም ድምፅ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ “አምላክ ንጹሕ ያደረገውን ነገር ርኩስ ነው ማለትህን ተው” አለው። 16 ይህም ለሦስተኛ ጊዜ ተደገመ፤ ወዲያውኑም ጨርቅ የሚመስለው ነገር ወደ ሰማይ ተወሰደ።
-