-
የሐዋርያት ሥራ 10:17-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ጴጥሮስ ‘የራእዩ ትርጉም ምን ይሆን’ በማለት በጣም ግራ ተጋብቶ እያለ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች የስምዖንን ቤት አጠያይቀው መጡና የውጭው በር ላይ ቆሙ።+ 18 ከዚያም ተጣርተው ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራው ስምዖን በዚያ በእንግድነት አርፎ እንደሆነ ጠየቁ። 19 ጴጥሮስ ያየውን ራእይ በሐሳቡ እያወጣና እያወረደ ሳለ መንፈስ+ እንዲህ አለው፦ “እነሆ፣ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል። 20 ስለዚህ ተነስተህ ወደ ታች ውረድ፤ የላክኋቸው እኔ ስለሆንኩ ምንም ሳትጠራጠር አብረሃቸው ሂድ።”
-