40 የኢየሱስንም አስከሬን ወስደው በአይሁዳውያን የአገናነዝ ልማድ መሠረት ጥሩ መዓዛ ባላቸው በእነዚህ ቅመሞች ተጠቅመው በበፍታ ጨርቅ ገነዙት።+ 41 እሱ በተገደለበት ቦታ አቅራቢያ አንድ የአትክልት ስፍራ ነበር፤ በአትክልት ስፍራው ውስጥ ደግሞ ገና ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር።+ 42 ዕለቱ አይሁዳውያን ለበዓሉ የሚዘጋጁበት ቀን+ ስለነበርና መቃብሩም በአቅራቢያው ይገኝ ስለነበር ኢየሱስን በዚያ አኖሩት።