ማቴዎስ 10:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ኢየሱስ እነዚህን 12ቱን የሚከተለውን መመሪያ በመስጠት ላካቸው፦+ “ወደ አሕዛብ አትሂዱ፤ ወደ ማንኛውም የሳምራውያን ከተማም+ አትግቡ፤ 6 ከዚህ ይልቅ ከእስራኤል ቤት ወደጠፉት በጎች ብቻ ሂዱ።+ የሐዋርያት ሥራ 3:25, 26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 እናንተ የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እንዲሁም አምላክ ለአብርሃም ‘የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ይባረካሉ’+ ብሎ ከአባቶቻችሁ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ወራሾች ናችሁ።+ 26 አምላክ አገልጋዩን ካስነሳ በኋላ እያንዳንዳችሁን ከክፉ ሥራችሁ በመመለስ ይባርካችሁ ዘንድ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው።”+ ሮም 1:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እኔ በምሥራቹ አላፍርምና፤+ እንዲያውም ለሚያምን ሁሉ+ ይኸውም በመጀመሪያ ለአይሁዳዊ+ ከዚያም ለግሪካዊ+ ምሥራቹ መዳን የሚያስገኝ የአምላክ ኃይል ነው።
5 ኢየሱስ እነዚህን 12ቱን የሚከተለውን መመሪያ በመስጠት ላካቸው፦+ “ወደ አሕዛብ አትሂዱ፤ ወደ ማንኛውም የሳምራውያን ከተማም+ አትግቡ፤ 6 ከዚህ ይልቅ ከእስራኤል ቤት ወደጠፉት በጎች ብቻ ሂዱ።+
25 እናንተ የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እንዲሁም አምላክ ለአብርሃም ‘የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ይባረካሉ’+ ብሎ ከአባቶቻችሁ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ወራሾች ናችሁ።+ 26 አምላክ አገልጋዩን ካስነሳ በኋላ እያንዳንዳችሁን ከክፉ ሥራችሁ በመመለስ ይባርካችሁ ዘንድ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው።”+