-
የሐዋርያት ሥራ 28:3-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ይሁን እንጂ ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ እሳቱ ውስጥ ሲጨምር ከሙቀቱ የተነሳ እፉኝት ወጥታ እጁ ላይ ተጣበቀች። 4 ባዕድ ቋንቋ የሚናገሩትም ሰዎች እፉኝቷ እጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ መሆን አለበት፤ ከባሕሩ ተርፎ በደህና ቢወጣም እንኳ ፍትሕ* በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ይባባሉ ጀመር። 5 እሱ ግን እፉኝቷን እሳቱ ላይ አራገፋት፤ አንዳችም ጉዳት አልደረሰበትም። 6 ሆኖም ሰዎቹ ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል ወይም ድንገት ወድቆ ይሞታል ብለው ይጠባበቁ ነበር። ብዙ ጠብቀው ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ይህ ሰው አምላክ ነው ይሉ ጀመር።
-