የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 13:50
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 50 ይሁንና አይሁዳውያን ፈሪሃ አምላክ ያላቸውን የተከበሩ ሴቶችና በከተማዋ የሚኖሩትን ታላላቅ ወንዶች በመቀስቀስ በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደት አስነሱ፤+ ከክልላቸውም አስወጧቸው።

  • 1 ቆሮንቶስ 15:30, 31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 እኛስ ሁልጊዜ ለአደጋ ተጋልጠን የምንኖረው ለምንድን ነው?+ 31 እኔ በየቀኑ ሞትን እጋፈጣለሁ። ወንድሞች፣ ይህ እውነት መሆኑን የጌታችን የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በሆናችሁት በእናንተ ላይ ባለኝ ትምክህት አረጋግጥላችኋለሁ።

  • 2 ቆሮንቶስ 11:23-26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 23 የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸው? እንደ እብድ ሰው ልናገርና እኔ ከሁሉ በላቀ ደረጃ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፦ ከሁሉም ይበልጥ ሠርቻለሁ፣+ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፣+ ብዙ ጊዜ ተደብድቤአለሁ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ሞት አፋፍ ደርሻለሁ።+ 24 አይሁዳውያን ለ40 ጅራፍ አንድ የቀረው ግርፋት አምስት ጊዜ ገርፈውኛል፤+ 25 ሦስት ጊዜ በዱላ ተደብድቤአለሁ፤+ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬአለሁ፤+ ሦስት ጊዜ የመርከብ መሰበር አደጋ አጋጥሞኛል፤+ አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባሕር ላይ አሳልፌአለሁ፤ 26 ብዙ ጊዜ ተጉዣለሁ፤ ደግሞም በወንዝ ሙላት ለሚመጣ አደጋ፣ ዘራፊዎች ለሚያደርሱት አደጋ፣ የገዛ ወገኖቼ ለሚያደርሱት አደጋ፣+ ከአሕዛብ ለሚሰነዘር አደጋ፣+ በከተማ፣+ በምድረ በዳና በባሕር ላይ ለሚያጋጥም አደጋ እንዲሁም በሐሰተኛ ወንድሞች መካከል ለሚያጋጥም አደጋ ተጋልጬ ነበር፤

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ